ዘላለም ወርቅአገኘሁ፤ ትሁቱ አራማጅ

18th November 2015  By Tedla D. Tekle
0


This article is available in English here.

ጸሐፊ፤ ተድላ ደስታ
ተርጓሚ፤ በፍቃዱ ኃይሉ

ጓደኛዬ ዘላለምን ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘ ሰው የሚረዳው ትህትናውን ነው፡፡ ይህ አስተያየት የሕሊና እስረኞችን እየተመላለሱ የሚጠይቁ ወጣት በጎ ፈቃደኞችን ጨምሮ፣ በአካል ያገኙት ብዙ ሰዎች አስተያየት ነው፡፡

ዘላለም ወርቅአገኘሁ ወይም እኛ እንደምንጠራው ዞላ ሰው አክባሪ፣ ጥንቁቅ እና አስተዋይ፣ በአዲስ አበባ ተወልዶ ያደገ የ32 ዓመት ሰው ነው፡፡ ከመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ጀምሮ በጉብዝናው የሚታወቅ ተማሪ ሲሆን በጎንደር ዩንቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪውን በቢዝነስ ማኔጅመንት ይዟል፡፡ ዞላ በትርፍ ጊዜው የእግር ኳስ ፕሪሚየር ሊጎችን መከታተልና የተቸገሩ ሰዎችን መርዳት ይወዳል፡፡ በተጨማሪም የሥራ ፈጠራ ችሎታውን ተጠቅሞ ራሱን እና ቤተሰቦቹን የሚረዱ ትናንሽ ቢዝነሶችን እየጀመረ ብዙ ጊዜ ተሳክቶለታል፡፡ ለተወሰኑ ዓመታት፣ ዞላ ከእኔ ጋር ስለ ኢትዮጵያ እና ስለአፍሪካ ቀንድ ጂኦፖለቲካዊ ጉዳዮች ጦማሮችን አዘጋጅቷል፡፡

ስለዞላ የማውቀው የሚከተለውን ነው፤ የየትኛውም ፓርቲ አይደለም፤ አልነበረምም፡፡ ነገር ግን፣ ጥልቅ ፖለቲካዊ ግንዛቤ ነበረው፡፡ ሁልጊዜም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወቅታዊ ሁኔታን ከሥር ከሥር ይከታተል እና በማኅበራዊ ሚዲያም ላይ በተለይ መረጃ እና ሐሳቦችን ለመለዋወጥ በንቃት ይሳተፍ ነበር፡፡ ነገር ግን ሥሙን መጠቀሙ የሚያስከትልበትን አደጋ በመፍራት ይጠቀም የነበረው በብዕር ሥም ነበር፡፡

ሐምሌ 1፣ 2006 በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ሲውል፣ ዘላለም በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ፐብሊክ አድሚኒስትሬሽን የማስተርስ ዲግሪ ፕሮግራም ተማሪ ነበር፡፡ ጥቅምት 21፣ 2007 ደግሞ ማኅበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ለሥርዓት ለውጥ የሚያሴር ግንቦት 7 የተባለ የተቃውሞ ቡድን ጋር ግንኙነት አለህ በሚል ክስ ተመሥርቶበታል፡፡ በተጨማሪም ሌሎችም መሰል ሕግ መተላለፎችም ተጠቅሰውበታል፡፡

ዞላ አሁን በይፋ ከሚታወቁ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ሀብታሙ አያሌው – የቀድሞው አንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት፣ ዳንኤል ሺበሺ – የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ፣ የሺዋስ አሰፋ – የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት አባል እና አብርሃ ደስታ – የመቀሌው ተቃዋሚ ፓርቲ አረና ትግራይ አባልና የመቀሌ ዩንቨርስቲ መምህር ጋር ከታሰረ ዓመት አልፎታል፡፡ ሁሉም የተከሰሱት በሱ ሥም በተከፈተ መዝገብ ነው፤ ይሁን እንጂ አንዳቸውንም ከመታሰሩ በፊት አያውቃቸውም፡፡ ምንም ዓይነት ግንኙነትም ከነርሱ ጋር አልነበረውም፡፡ ሦስት ሌሎች የዞላ ጓደኞችም በአንድ አሜሪካን አገር የሚኖር ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ በኩል መጥቷል የተባለ የኢንተርኔት ደኅንነት ሥልጠና ላይ ለመገኘት በማመልከታቸው አብረውት ታስረዋል፡፡ ነገር ግን፣ ሥልጠናው ጨርሶ አልተካሄደም፡፡ ለብዙ ፖለቲከኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ሰዎች፣ የዚህ ወጣት ከፍተኛ ሥም ካላቸው የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር አብሮ መከሰስ አስገራሚ ክስተት ሆኖባቸዋል፡፡

ዘላለም ከላይ የጠቀስኩትን ማስተርስ ዲግሪውን መሥራት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ግንኙነታችን እየቀነሰ መጥቶ ስለነበር፣ ባለፈው ዓመት የእስሩ ዜና ሲመጣ በጣም ነው ያስደነገጠኝ፡፡ በሐሳቤ የሚመላለስብኝ በዚህ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ፊቱ ላይ የሚነበበው ወኔ እና ሊጠይቁት የሄዱት በጎ ፈቃደኞች የገለጹልኝ ትህትናው ነው፡፡

ጓደኛዬ ዞላ፣ ልቤ ነጻ ሆነህ ማየትን ይናፍቃል!

 
Tedla D. Tekle
Tedla, PhD, worked for several private media outlets when he was in Ethiopia. He blogs on De Birhan and other media outlets, and spreads awareness about his co-blogger and friend Zelalem Workagegnehu, who has been jailed in Ethiopia since July 2014. View articles by Tedla here. Web www.debirhan.com Twitter: @debirhanerYou might also like
Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


More Story
The Psychology of Rape In many countries, a culture of rape is woven into the very fabric of society. In countries of war, the unimaginably traumatic...