እገዛ እና ድጋፍ

1st March 2017  By Melody Sundberg
0


This article is translated from English. Read the original here.

የማሰቃየት ተግባር ተፈጽሞብዎ ያውቃል? ከዚህ ህመም ለመዳን ሊረዳዎት የሚችል እገዛና ድጋፍ ማግኘት ይፈልጋሉ? በስዊድን የሚከተሉት ድርጅቶች የማገገሚያ አገልግሎቶችን ይሰጣሉ፡፡

Röda korsets center för torterade flyktingar i Stockholm (በቀይ መስቀል የማሰቃየት ተግባር የተፈጸመባቸው  ስደተኞች መርጃ ማዕከል በስቶክሆልም )

 መረጃ በስዊዲንኛ፤ http://www.redcross.se/rkcstockholm
መረጃ በእንግሊዝኛ ፤ http://www.redcross.se/contentassets/346eb967a7894dd09c52509adfa264f1/ny-infoblad-engelska.pdf
መረጃ በትግሪኛ፤ http://www.redcross.se/contentassets/346eb967a7894dd09c52509adfa264f1/infoblad_tigrinja151117.pdf
ስለቀይ መስቀል የማሰቃየት ተግባር ሰለባዎች ማገገሚያ በስዊድንኛ የቀረበ ዘገባ  http://www.redcross.se/globalassets/dokument/vard-och-behandling/rodakorset_arsbok-vard-2015_version-2.pdf

Röda Korsets behandlingscenter för krigsskadade och torterade (በቀይ መስቀል ከጦርነት እና ከማሰቃየት ተግባር የተረፉ ሰዎች ህክምና ማዕከል)
መረጃ በስዊዲንኛ፤ http://www.redcross.se/behover-du-var-hjalp/vard-och-behandling/
የሚገኝበት ቦታ፤ ማልሞ፣ ዮተባሪ፣ ዑፕሳላ፣ ሾቭደ፣ ሸለፍቴ እና ስቶክሆልም

Kris-och Traumacentrum (ጉዳት እና ቀውስ መርጃ ማዕከል)
መረጃ በስዊዲንኛ፤ http://krisochtraumacentrum.se/
በስቶክሆልም ይገኛል፡፡

በስዊድን ከማሰቃየት ተግባር በሕይወት የተረፉ ሰዎች ማገገሚያን በተመለከተ አጠቃላይ መረጃ፤ http://www.viss.nu/Handlaggning/Vardprogram/Psykisk-ohalsa/Patienter-som-varit-utsatta-for-tortyr/

 ጥቂት መረጃ ስለ የማሰቃየት ተግባር 

የማሰቃየት ተግባር  ተፈጽሞብዎት ያውቃል? በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ አልፈው በሕይወት ተርፈዋል። እንደ እርሰዎ በተመሳሳይ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያለፉ ሌሎች በርካታ ሰዎች አሉ። ብቻዎን አይደሉም! ከህመምዎ እንዲድኑ እገዛ የሚያደርጉ የበየነ መረብ መረጃዎች  እና መጻሕፍት አሉ። መረጃን ማንበብ ሊያጋጥምዎት ስለሚችሉ ስሜቶች እና አፀፋዊ ምላሾች ለመረዳት ያግዛል። የእርስዎን ስሜት ሌሎች ብዙ ከማሰቃየት ተግባር የተረፉ ሰዎች የሚጋሩት መሆኑን ማወቁ ደግሞ ጥሩ ነው። የባለሙያ እርዳታ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከማሰቃየት ተግባር በሕይወት የተረፉ ሰዎች ከህመማቸው እንዲድኑ የሚረዱ ድርጅቶች አሉ (ስዊድን ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ ከላይ ያለውን መረጃ ይመልከቱ)።

ለማሰቃየት ተግባር  መዳረግ ማለት ለአንድ ከአይምሮ የማይጠፋ የጉዳት ስሜት መዳረግ ማለት ነው። የአሜሪካ የሥነ ልቦና ማኅበር እንደገለጸው፣ “የጉዳት ስሜት እንደ አደጋ፣ አስገድዶ መደፈር ወይም የተፈጥሮ መቅሰፍት  ያሉ አስፈሪ ኹነቶች የሚሰጥ ስሜታዊ ምላሽ ነው። ከዚህ ክስተት በኋላ ድንጋጤ እና ክስተቱን መካድ ዓይነተኛ አፀፋዊ ምላሾች ናቸው። የረጅም ጊዜ አፀፋዊ ምላሾች ከሚባሉት ዉስጥ ያልተገመቱ ስሜቶች፣ ምልሰቶች፣ የሻከረ ግንኙነት እና እንዲሁም ራስ ምታት ወይም ማቅለሽለሽ የመሳሰሉትን አካላዊ ምልክቶች ይጨምራል።”

አንዳንድ ሰዎች አፀፋዊ ምላሻቸውን እነሱ ከተዳረጉበት የማሰቃየት ተግባር ጋር ማገናኘት ከባድ እንደሆነ ይሰማቸዋል። በስዊድን ጉዳት እና ቀውስ መርጃ ማዕከል (Crisis and Trauma Centre) እንደ ጠቆመዉ እርዳታ ለማግኘት እነሱን ያነጋግሩቸው ብዙ ሰዎች “እብድ እንዳይሆኑ” ያለባቸውን ፍርሃት ገልጸዋል። ሆኖም ግን አብዛኛውን ጊዜ እነዚህ ሰዎች እያጋጠማቸው ያለው ነገር እነርሱ ለተዳረጉበት የማሰቃየት ተግባር የተዳሩ ሰዎች የሚያሳዩት የተለመዱ አፀፋዊ ምላሾች ናቸው።

አንድ ለማሰቃየት ተግባር የተዳረገ ሰው ብዙ ዓይነት ስነ ልቦናዊ እና አካላዊ ምልክቶች ሊያጋጥመው ይችላል። ለአንዳንድ ሰዎች ምልክቶቹ ለጉዳት ከተዳረጉ በኋላ ወዲያውኑ ይታያሉ። ለሌሎች ግን የህመሙ ምልክቶች መታየት እስኪ ጀምሩ ዓመታት ሊወስድ ይችላል። በዚህ ወቅት የህመሙ ምልክቶች አብዛኛውን ጊዜ ከሚያስጨነቅ ኹነት ጋር በተያያዘ ይጀምራሉ።    በአንዳንድ ሁኔታዎች ደግሞ ስነ ልቦናዊ የህመም ምልክቶቹ ከስቃይ ጋር የተያያዙ ህመሞች የምርመራ ውጤት መስፈርቶችን ያሟላሉ። የተለመዱ ከስቃይ ጋር የተያያዙ ህመሞች የሚባሉት፡-

  • ስቃይን ተከትሎ የሚመጣ የጭንቀት በሽታ(Post Traumatic Stress Disorder, PTSD)፣ ይህ በጣም የተለመደ በሽታ ነው።
  • ኃይለኛ የጭንቀት በሽታ (Acute Stress Disorder)
  • የመንፈስ ጭንቀት በሽታ
  • ድብርት

ከየማሰቃየት ተግባር ጋር የተያያዙ በሽታዎችን ለማከም ብዙ ዓይነት ዘዴዎች  አሉ። አንዳንድ ሰዎች በራሳቸዉን በማከም ወይም በአጋዥ አከባቢ ይድናሉ። ይሁን እንጂ ከነዚህ በሽታዎች ውስጥ ብዙዎቹ የባለሙያ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። ለምሳሌ ስቃይን ተከትሎ የሚመጣ የጭንቀት በሽታ (PTSD) ሕክምና ብዙ ጊዜ በኮግንቲቭ የጠባይ ሕክምና [Cognitive Behavioral Therapy] ነው የሚታከመው። ይህ ሕክምና በተደጋጋሚ የሚታዩ ሃሳቦችን፣ ጠባዮችንና በሽታዎችን የሚቀሰቅሱ አስተሳሰቦችን በመለወጥ የሚደረግ ህክምና ነው።

ስለ የማሰቃየት ተግባር እንዲሁም ስለ የጥቃቱ ሰለባዎች የምስክርነት ቃል የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣ Untold Stories ድረ ገፅ ላይ ይህን በመጫን ያገኛሉ።ተጨማሪ
የመረጃ ምንጮች

የማሰቃየት ተግባር ሰለባዎች መርጃ ማዕከል http://www.cvt.org/
ወሲባዊ ጥቃት መከላከያ እና ግንዛቤ ማስጨበጫ ማዕከል: https://sapac.umich.edu/

 
Melody Sundberg
Project manager of Untold Stories. Photographer and artist. Educated in Psychology.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


More Story
Jailed Journalist Elias Gebru Needs Justice and Medical Help Ethiopian freelance journalist Elias Gebru worked as an editor for many newspapers and magazines. He also advocated for free...