ሕይወቴን የለወጠ መጽሐፍ አነበብኩ

4th July 2016  By Melody Sundberg
0


(ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ የተተረጎመ)

ውድ አንባቢ፣

ሕይወቴን የለወጠ መጽሐፍ አነበብኩ፡፡

የተደጋገመና የሰለቸ አባባል እንደሆነ አውቃለሁ፤ ነገር ግን ስለመጽሐፉ በሌላ መንገድ መናገር ዝቅ አድርጎ የመግለጽ ያህልይሰማኛል፡፡

በፌብሩዋሪ 2014 ከሬዲዮ አንዳች ነገር ለማዳመጥ ፈልጌ ነበር፡፡ ነገር ግን በአጋጣሚ “438 ቀናት” በሚል ርዕስ በስዊድናውያኑጋዜጠኞች ማርቲን ሽብዬና ጆሀን ፐርሰን የተጻፈው መጽሐፍ የድምፅ ቅጂን አገኘሁ፡፡ ምናልባትም አንዳንዶቻችሁ ግጭት ወዳለበትየኢትዮጵያ ምሥራቃዊ ክፍል ወደሆነው ኦጋዴን ምን እየተከሰተ እንደሆነ ለመዘገብ ስለሄዱት ጋዜጠኞች ሰምታችሁ ይሆናል፡፡ ከዚሁአካባቢ በሰብኣዊ ፍጡር ላይ ስለሚፈፀሙ ወንጀሎች በተደጋጋሚ ወሬዎች ይሰማሉ፤ በተጨማሪም በአካባቢው ነዳጅ ለመፈለግየተሰማሩ ኩባንያዎችም ነዋሪውን ሕዝብ በአሉታዊ መልኩ እየጎዱት ነው፡፡

የትኛውም ጋዜጠኛ ወደኦጋዴን እንዲገባ ስለማይፈቀድለት በዚያ አካባቢ ምን እየተከሰተ እንደሆነ ለማወቅ አዳጋች ነው፡፡ እውነቱንለማወቅ የፈለጉት ማርቲን እና ጆሀን የሶማሊያን ድንበር አልፈው ወደኢትዮጵያ ዘለቁ፡፡

ነገር ግን በኋላ ላይ እንደገለጹት ስለነዳጅ ዘይት ያሰቡት ዘገባ ፊቱን አዙሮ ስለብዕር ሆኖ አገኙት፡፡

እነዚህ ስዊድናዊ ጋዜጠኞች ሳያስቡት የኢትዮጵያ መንግሥት ሐሳባቸውን በነጻነት በሚገልፁ ሰዎች ላይ በከፈተው ዘመቻ መሐልላይ እራሳቸውን አገኙት፡፡ ማርቲንና ጆሀን ተይዘው በሽብርተኝነት ተከሰሱ፡፡ በእስር ቤት ቆይታቸውም ብቻቸውን እንዳልሆኑተረዱ፡፡ ሥራቸውን ስለሠሩ ሽብርተኛ ተብለው የታሰሩ ጋዜጠኞችን አገኙ፡፡ በ2012 ማርቲንና ጆሀን ይቅርታ ተደርጎላቸው ወደስዊድን ሲመለሱ ኢትዮጵውያኑ ጋዜጠኞች እዚያው እስር ቤት ቀሩ፡፡

ያነበብኩትን እንደዋዛ ልረሳው አልቻልኩም፡፡ በከፋ ሁኔታ በእስር ቤት እየማቀቁ ስለሚገኙ ስለእነዚህ ንጹሃን ሰዎች ማሰብንአእምሮዬ ፈፅሞ ሊተው አልቻለም፡፡ ኢትዮጵያውያኑ ጋዜጠኞች ስለኢፍትሓዊነት፣ በሰዎች ላይ ስለሚፈፀም ሰቆቃና ስለንጹሃንበእስር ስለመንገላታት ነበር የጻፉት፡፡ በሥራቸው  ላይ ስለሚያደረጉ ቅድመ ምርመራ፣ ሠላማዊ ሰልፍ ስለማድረግ መብት እናበዴሞክራሲያዊ መብቶች ላይ መንግሥት ስለሚያደርገው አጠቃላይ ተፅዕኖ እየተቹ ይጽፉ ነበር፡፡ ይህን በማድረጋቸውምመብቶቻቸውን ተነጥቀው እንደአገር ከጂ ተቆጥረዋል፡፡ ተራ ዜጎችም ቢሆኑም “አይሆንም” ብለው ደፍረው ለመናገር ደፋር ወንድናሴቶች ናቸው፡፡

ግን እነዚህ ሰዎች ከእኛ በምን መልኩ የተለዩ ናቸው? ውድ አንባቢ ከእርስዎስ፤ ከእኔስ በምን ይለያሉ? በምንም አይለዩም፡፡

ስዊድን ውስጥ እየኖርኩ ሐሳብን መግለጽ የተለመደና ተቀባይነት ያለው የዕለት ተዕለት የኑሮ አካል መሆኑን አሰብኩ፡፡ ብሎግ ላይበመጻፍ፣ ከጓደኞች ጋር በመወያየት ወይም በመጽሔቶች ላይ ሁሉም ሰው ሐሳቡን ይገልጻል፡፡ ፖለቲከኞች ስህተት ፈፅመዋል ብለንካሰብን ስለጉዳዩ ከሌሎች ጋር መወያየትን እንወዳለን፡፡ ታዲያ ይህንን ለማድረግ መብት የለንም? በሚገባ አለን እንጂ! ሐሳብንበነጻነት መግለጽ ከመሠረታዊ ሰብኣዊ መብቶች መካከልም አንዱ ነው፡፡

መጽሐፉን ሳነብ ግን፣ እኔ ያለኝ ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት የቅንጦት ያህል መሆኑን ተገነዘብኩ፡፡ ሁሉም ሰው ሐሳቡንበነጻነት ለመግለጽ በሚቻልበት አገር ውስጥ የመወለድ ዕድል ላይገጥመው ይችላል፡፡

እኔም ሐሳብን በነጻነት ስለመግለጽ መታገል በጀምርኩበት ጊዜ፣ “ጋዜጠኝነት አሸባሪነት አይደለም” የሚል በጣም ቀላል የሆነመልዕክት ይዤ ነበር የተነሳሁት፡፡ ሐቁን መናገር ስጀምር ተጨባጭ የሆነ ተፅዕኖ ይኖረኛል ብዬ ከፍ ያለ ግምት አልነበረኝም፡፡መልዕክቶቼንም የሚያነባቸው ሰው ይኖራል ብዬም አላሰብኩም፤ ነገር ግን አንድ ነገር ማድረግ እንዳለብን ይሰማኝ ነበር፡፡ የእኔእምነትም ማንም ሰው በተሳሳተ ሁኔታ ታስሮ፣ ቢያንስ አንድ ሰው ስለተፈፀመበት ኢፍትሐዊነት ተረድቶ “ልክ አይደለም” ብሎየሚናገርለት ሳይኖር እንዳይቀር ማድረግ ነው፡፡

የሞባይል መልዕክት ድምፅ

የተላከው መልዕክት፤ “ስለምታደርጊው ነገር ምስጋና ይድረስሽ፡፡ በጀመርኩት እንድቀጥል አበርትተሸኛል፡፡ ከስደተኛ ጋዜጠኛ”፡፡

የሞባይል መልዕክት ድምፅ መምጣቱን ቀጥሏል፡፡

“ስለታሰሩት ጓደኞቼ ስለምታደርጊው ሁሉ አመሰግናለሁ፡፡”

“ስለምን ስለኛ እንዲህ ተጨነቅሽ?”

“እኛን ስላጋጠመን ነገር እንዴት ልታውቂ ቻልሽ?”

መልዕክቶቹን የሚጽፉልኝ እኒዚህ ሰዎች ኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈፅሙትን ኢፍትሐዊነትን ሲጋፈጡ የነበሩ ናቸው፡፡ እራሳቸውንለሰቆቃና ለእስር አጋልጠው የሰጡ ነበሩ፡፡ ምንም እንኳን ሊገጥማቸው የሚችለውን ችግር ቢያውቁም ለሌሎች በመቆምሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠዋል፡፡ አሁን ግን ተገቢ ያልሆነ እስርን ለማምለጥ ሲሉ አገራቸውን፣ ቤተሰባቸውን እና ጓደኞቻቸውንጥለው ለመሰደድ ተገድደዋል፡፡

በዚያች አገር ደፍረው የሚናገሩና የሚጽፉ ቁጥራቸው እየቀነሰ ነው፡፡ ከነበሩት መካከል ብዙዎቹ በኢትዮጵያ እስር ቤቶችተዘግቶባቸዋል፡፡ ሌሎቹ ደግሞ በመጨረሻዋ ሰዐት ላይ ለማምለጥ ችለው በስደት ይኖራሉ፡፡ እነዚህ ናቸው የምስጋና መልዕክቶቹንየሚልኩልኝ፤ እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡ ግን እኔ አይደለሁ እንዴ እነሱን ማመስገን ያለብኝ?

የታሰሩት ነበሩ ነጻ እንድንወጣ ሲታገሉልን የነበሩት ሲል ነበር ማርቲን ሺብዬ፡፡

ትክክል ነው፡፡

*የሞባይል መልእክት ድምፅ*

የተላከው መልዕክት፤ “ብናገኝሽ ደስ ይለናል”

ኦገስት 2014፡፡ ስዊድን ውስጥ በስደት የሚኖሩ ሁለት ጋዜጠኞችን ለማግኘት ስቶክሆልም ዋናው ባቡር ጣቢያ ተገኝቻለሁ፡፡ ከዚህበፊት አግኝቻቸው ስላማላውቅ የተረበሸ ስሜት ይሰማኛል፡፡ ቀደም ሲልም በስደት ከሚኖሩት ጋዜጠኖች መካከል አንዳቸውንምአግኝቼ አላውቅም፡፡ አንደኛው ቀድሞ መጣ፡፡ ትንሽ ዓይናፋር ይመስላል፤ ፈገግታው ቆጠብ ያለ ነው፡፡ ተቃቅፈን ሠላም ተባባልን፡፡ሌላኛውም ጋዜጠኛ ጥቂት ቆይቶ መጣ፡፡

እምባዬን ለመቆጣጠር እየታገልኩ ነው፡፡ እነዚህ ሁለት ሰዎች ያለፉበትን ሁኔታ መረዳት አጅግ አስቸጋሪ ነው፡፡ ለእኔ ታሪካቸውከሞላ ጎደል ልቦለድ የሚመስል ሲሆን፣ ከእነርሱ አንፃር ምን ያህል በተመቻቸ ሁኔታ ውስጥ እንደምኖር ተገነዘብኩ፡፡ ነጻነትበሰፈነበት አገር እኖራለሁ፡፡ ለዚህም ምስጋናዬን ለማቅረብ አስቤ አላውቅም፡፡ እነዚህ አጠገቤ ያሉት ግለሰቦች ግን ለማምለጥባይችሉ ኖሮ እስር ቤት ይወረወሩ እንደነበር ሳስበው ለመቀበል ይከብደኛል፡፡

ውድ አንባቢ፤

እነዚህን አንዳይናገሩ ስለተደረጉ ሰዎች ያልተነገሩ ታሪኮችን ላካፍላችሁ እፈልጋለሁ፡፡ ይህም የእኔ ኃላፊነት እንደሆነ ይሰማኛል፡፡

ሜሎዲ ሰንድበርግ
Melody Sundberg
Project manager of Untold Stories. Photographer and artist. Educated in Psychology.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


More Story
ሠዎችን ክፉ የሚያደርጋቸው ምንድን ነው? በአቤል ዋበላ ከእንግሊዘኛው የተተረጎመ የማሰቃየት ተግባር (Torture) ጭቆናን...