የኦጋዲን የጨቋኝነት መረብን መስበር

22nd May 2017  By Aden Hassan
0


Translated from English

ምንም እነኳን በኢትዮጵያ የሚገኘው የሱማል(ኦጋዴን) ክልል እጅግ ጨቋኝ ከሆኑ አካባቢዎች አንዱ ቢሆንም በአለም አቀፍ ደረጃ ይሄ ነው የሚባልትኩረት አላገኘም፡፡ ጅምላዊ ቅጣት የተለየ ሳይሆን የተለመደ ድርጊት ሆኗል፡፡ የክልሉ ፕሬዝዳንት አብዲ ሞሀመድ ኦማር እንደ ብረት ቀጥቅጦየመግዛት ዝናው ጅምላ ግድያ፣ አፈና እና የመግደል አባዜ እንዲሁም የተቃዋሚ ቤተሰቦችን/ዘመዶችን ማሰር ያካተተ ነው፡፡ ውስጣዊ ተቃውሞለማርገብ በህዝቡ ላይ ጥቃት ለማድረስ የተለየ ፍላጎት ያለቸውን ልዩ ፖሊስ የተባለውን ጦር አሰማርቷል፡፡ ለተቃዋሚዎች ካለው ኃይለኛ ትግስትአልበኝነት ጋር ተዳምሮ የአብዲ ሞሀመድ ኦማር ጭፍን የበቀል እርምጃ የሚገባቸው በሚል የመዘገባቸው የተቃዋሚዎች ዝርዝር ብዙ ናቸው፡፡

እየተፈፀመ ባለው ዘግናኝ የሰብአዊ መብት ጥሰት ምክንያት ብዙ ሰዎች ክልሉን ለቀው ተሰደዋል፡፡ አብዛኛዎቹም በአሁን ሰአት በምእራባዊ ሀገራትየሚኖሩ እና ፕሬዝዳንቱ የሚፈጽመውን ያልተገባ ድርት የሚቃወሙ ናቸው፡፡ ነገር ግን ፕሬዝዳንቱ ተቃዋሚ ዲያስፖራዎችን ዝም ለማስባል ባህርተሻግረው መረጃ የሚያቀበሉትን ሰላዮች አሰማርቷል፡፡

በአብዛኛው መረጃ አቀባዮቹ የምእራባዊ አገር ዜግነት ያላቸው እና ይህም ያመጣላቸውን ነፃነትና እድል በመጠቀም በህዝቡ ላይ ጉዳት በማድረስእድሜውን ያራዘመውን መንግስት እንዳይወድቅ ድጋፍ ሆነውታል፡፡ በአውሮፓ፤በአውስትራልያ እና በሰሜን አሜሪካ ጥገኝነት በማግኘትየተሰጣቸውን ነጻነት በመጠቀም የሌሎችን ተመሳሳይ መብት ለመንጠቅ እየሰሩ ይገኛል፡፡

ህዝቡም ድምጹን እንዳያሰማ የተገደደው ሰላማዊ ሰልፍ መሳትፍ ማለት ኢትዮጵያ ያላለው ዘመዱ የሞት ቅጣትእንደሚጠብቀው ስለሚያውቅ ነው፡፡

ያለምንም ፍርድ ሺዎች ታስረዋል፡፡ህዝቡም በቁጥጥር ስር ስለዋሉ ዘመዶቻችው ድምጻቸውን ማሰማት ይፈልጋሉ፡፡ ነገር ግን ህዝቡ ሰላማዊሰልፎችን በሜኔሶታ፤ ለንደን እና በሌሎች ቦታዎች ሲያደርግ ጥቃት፤ማንጓጠጥ እና ማስፈራራት በፕሬዝዳንቱ መረጃ አቀባዮች ይደርስባቸዋል፡፡በቅርቡ ሂውማን ራይት ዎች ባወጣው ሪፖርት ተመሳሳይ በደል የደረሰባቸው እና በተደራጀ መልኩ በቡድን ጉዳት የደረሰባቸው ተጠቂዎች የሰጡትምስክርነት ተጠናቅሯል፡፡ በፈረንጆች 2016 . መግቢያ አብዲ ሞሀመድ ኦማር አውስትራልያን በጎበኘበት ወቅት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍተካሂዶ ነበር፡፡ መረጃ አቀባዮቹ ሀገር ቤት ያሉ የሰልፈኞችን ዘመዶች ለመቅጣት ሰልፈኞቹ እነማን እንደሆኑ አጣርተው ሪፖርት እንዲያደርጉማስፈራርያ ተደርጎባቸው ነበር፡፡ በትክክልም የሆነው ይሄ ነበር፡፡ሰላማዊ ሰልፍ በወጡት ሰዎች ላይ የበቀል እርምጃ ወድያውኑ ተወሰደ፡፡ቤተሰቦቻቸው እና ዘመዶቻቸው ወዲያውኑ በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

እንዲህ አይነት ድርጊት አንዴ ብቻ የተፈጸመ አይደለም፡፡ በምእራቡ አለም ባሉ ሀገራት በተደራጀ መልኩ እየተፈጸመ ያለ ነው፡፡ መረጃ አቀባዮቹህዝባዊ ስብሰባዎች ላይ በመገኘት ንግግር የሚያደርጉ ሰዎችን በሚስጥር ይቀዳሉ፡፡ የተቃውሞ ስብሰባዎችን በድብቅ በመግባት ሰላማዊ ሰለፎችንበቪዲዮ ይቀርጻሉ፡፡ ሰልፈኞችን በመቃወም ሰልፍ እየጠሩ ተቃዋሚ ሰልፈኞችን ፎቶ ያነሳሉ፡፡ከዛም መረጃዎቹን ለአብዲ ሞሀመድ ኦማር እና ጭፍንደጋፊዎቹ በመላክ ከሰልፉ ጋር ምንም ግኑኝነት የሌላቸው የሰልፈኞች ዘመዶች ላይ ቅጣት እንዲፈጸም ያደርጋሉ፡፡ ወላጆች፣ እህት ወንድም፣ የአክስአጎት ልጆች እና ሌሎች የቅርብ ዘመዶች ወድያውኑ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ፣ እንዲታሰሩ፣ ንብረታቸው እንዲወረሱ እና አንዳንዴም እንዲገደሉይደረጋል፡፡ መድፈር እና በሴቶች ዘመዶቻቸው ላይ እንደሚፈጸም ማስፈራራት እጅግ በተጠናከረ እና በተደራጅ መልኩ የሚጠቀሙበት መሳርያነው፡፡ እህታቸው እና የአክስት አጎት ልጅን እንደሚደፍሩ ተቃዋሚዎችን ማስፈራራት የተለመደ ነው፡፡

የህዝብ ድምጽን ብቻ በማፍን ውጤታማ የሆነ የከፋ አገዛዝ ነው፡፡ ህዝቡም ድምጹን እንዳያሰማ የተገደደው ሰላማዊ ሰልፍ መሳትፍ ማለትኢትዮጵያ ያላለው ዘመዱ የሞት ቅጣት እንደሚጠብቀው ስለሚያውቅ ነው፡፡ ሀሳብን በነጻነት መግለጽ የተፈጥሮ መብት በሆነባቸው የምእራባውያንከተማ መንገዶች በሚገርም ሁኔታ የሰባዊ መብት ጥሰት በሚፈጽሙ በአብዲ ሞሀመድ ኦማር መረጃ አቀባዮች ምክንያት ሀሳብን በነፃነት መግለጽአደገኛ ሆኗል፡፡ ምእራባውያን ባለስልጣናትም ይህ ተቋማዊ ጥቃት አውራ ጎዳናዎቻቸው እና መንገዶቻቸው እያስተናገዱ መሆኑን ሊያውቁ ይገባል፡፡የአሜሪካ፣ የአውስትራሊያ እና የአውሮፓ ዜጎች ባደጉበት ከተማ ከባድ የአካል እና የስነ ልቦና ጥቃት እየደረሰባቸው ነው፡፡ የዲሞክራሲ መብቶቻቸውበአንባገነናዊ መሳርያዎች ስጋት ውስጥ ገብተዋል፡፡ ቤተሰቦቻቸው ተገለዋል፣ያሉበት አይታወቅም ወይም በታዋቂ የኦጋዴን ማረሚያ ቤቶች ፍርድ ቤትሳይቀርቡ ታስረዋል፡፡በገዢው እና በአሻንጉሊት ተከታዮቹ የሚደርሰው ይህ ጥቃት አዲስ አይደለም፡፡ሂውማን ራይት ዎች እና አምነስቲ ኢንተርናሽናልእና ሌሎች የሰባዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ላለፉት አመታት ሲፈጸም የነበረውን ጥሰት ዘግበዋል፡፡ በፈረንጆቹ 2006 . መግቢያ በእነዚህድርጅቶች እነደተዘገበው የጥሰቱ ደረጃ የተዛባ እና ያልተመጣጠነ እንደሆነ ተዘግቧል፡፡

 

መረጃ አቀባዮችን ማጋለጥ

መረጃ አቀባዮች፣ የልዩ ፖሊስ አዛዦች እና የአገዛዙ ተወካዮች በምእራባዊ ሀገራት የፖለቲካ ጥገኝነት ይሰጣቸዋል፡፡ ይሄ መቆም አለበት፡፡ የመረጃመረባቸውን ለመበጣጠስ ዘመቻ ተካሂዷል፡፡ የመጀመርያ እርምጃ የሚሆነው የመረጃ አቀባዮችን ማንነት ማጥናት ነው፡፡ በሁለተኛነት የክልሉመንግስት የሚያደርሰውን ጥቃት እና የሰብአዊ መብት ጥሰት በማገዝ እና በማበረታታት ተጠያቂ እንዲሆኑ ህጋዊ እና ፖለቲካዊ ተጽኖ በመሪዎች ላይማድረግን ይጠይቃል፡፡ዲሞክራሲ እና ነጻነትን ተጎናጽፈው በምእራባዊ ሀገራት ጥገኝነት ያገኙ እና በላካቸው መንግስት ጥቅም የሚያገኙ ግለሰቦችሌሎች ሰዎች ተመሳሳይ የመናገር ነጻነት እና ክብር እንዲነፍጉ መፈቀድ የለበትም፡፡ እነዚህን ተጠያቂ ለማድረግ  መረጃ አቀባዮቹ ማን እንደሆኑ እናእረዳት የሌላቸው ንጹሃን ዜጎች ላይ የሚፈጽሙትን ድርጊት የአሜሪካ እና የአውሮፓ መንግስታት እንዲያውቁ ቋሚ እና ቀጣይነት ያለው ዘመቻይደረጋል፡፡ ምእራባዊ ሀገራት ለእነዚህ ሰዎች የሰጡትን ዜግነት እሰከ መንጠቅ መድረስ አለባቸው፡፡ ምክንያቱም የተሰጣቸው መብቶች በጥላቻየተመሰረተ የሰብአዊ መብት ጥሰት ለመፈጸም የለአግባብ ተጠቅመውበታል፡፡ የለንደን፣ የሜልቦርን እና የሚኒአፖሊስ መንገዶች እንደ በፊቱ አብዲሞሀመድ ኦማርን ለመቃወም ሰላማዊ አይደሉም፡፡ ነገር ግን በቅርቡ መረጃ አቀባዮቹም በቅርቡ አደገኛ መሆናቸው አይቀርም፡፡

 

ይህ ጽሁፍ መጀመርያ በህዳር 1 ቀን 2016 . በፊስ ቡክ ገጽ ላይ የተለቀቀ ቢሆንም ታርሞ እና በጸሀፊው ፍቃድ የታተመ ነው፡፡

*ልዩ ፖሊስ በኦጋዴን ክልል የኢፌዲሪ መንግስት በሚያሰተዳድረው በኢትዮጵያ ጦር የሚመራ ነው፡፡ የኦጋዴን ክልል ፕሬዝዳንት በልዩ ፖሊስ እናበብሔራዊ ጦር መካከል ያለ ሰው ነው፡፡Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


More Story
በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ፍትህ እና የህክምና እርዳታ ያስፈልገዋል፡፡ Translated from English by Meron Mesfin. ኢትዮጵያዊው ፀሀፊ እና ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ በብዙ...